"የጎዳና ላይ ሻወር" ተብሎ የሚታውቀው የበጎ ፈቃደኞች ቡድን፣ በዐዲስ አበባ ከተማ "አሜሪካን ግቢ" እየተባለ በሚጠራው ሰፈር፥ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን ገላ እያጠበ ንጹሕ ልብስ በማልበስ፣ በማሳከም እና በመመገብ፣ እንዲሁም ለማደሪያቸው አነስተኛ ተንቀሳቃሽ የቆርቆሮ ቤት ሠርቶ በመለገስ ይታወቃል። በተጨማሪም ቡድኑ፣ ...